ራሚስ ባንክ አ.ማ
የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 2,101,106,460.00 |
የባንኩ ምዝገባ ቁጥር፦ MT/AA/3/0053691/2015 |
የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 636,084,429.57 |
የባንኩ አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 09፣ የቤት ቁ 059 |
ራሚስ ባንክ (አ.ማ.) የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ 1ኛ መደበኛ እና 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 23 ቀን 2016 ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሚሌንየም የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የባንካችን ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-
1. የጉባዔውን ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየም፤
2. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
3. እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
4. እ.ኤ.አ የ2022/23 በጀት ዓመት የባንኩን የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
5. የባንክ ምሥረታ ቀሪ ሥራዎች በተመለከተ የአደራጆች ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
6. እ.ኤ.አ የ2023/24 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል እና አመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን፤
7. የባንኩን አክሲዮን ገዝተው ከምሥረታ ጉባዔው በፊት ያልፈረሙትን ግለሰቦች ባለአክሲዮንነት ማጽደቅ፣
8. እ.ኤ.አ የ2023/24-2025/26 ቀጣይ ሶሰት ዓመት የውጭ ኦዲተር መሰየምና የሥራ ዋጋቸውን መወሰን፣
9. የተጓደሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ማሟላት፣
10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም፣
11. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላት የጥቆማ እና የምርጫ ሂደት አፈፃፀም መመሪያ ማጽደቅ፣
12. የተቆጣጣሪ ቦርድ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
13. ለተቆጣጣሪ ቦርድ አባላት የሚከፈለውን የሥራ ዋጋና የአበል መጠን ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
14. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፤
የባለአክሲዮኖች 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-
1. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
2. የባንኩን አክሲዮን ገዝተው ቀሪ ክፍያ ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች ቀሪ ክፍያ ከፍለው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ መወሰን፣
3. የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በቦርዱ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
4. የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ ለማሻሻል በቦርዱ የቀረበውን ረቂቅ ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
5. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፤
ማሳሰቢያ፡-
§ በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት የስራ ቀናት በፊት ቦሌ መንገድ፣ ፍላሚንጎ የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ፕረዝደንት ቢሮ ፊት ለፊት፣ ራሚስ ባንክ ሕንፃ፣ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት የእንደራሴ (Proxy) ቅጽ በመሙላት በምትወክሉት ወኪል አማካይነት በጉባዔው ላይ መሳተፍና ድምጽ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
§ እንዲሁም፣ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ በሚቀርብ ወኪል በኩል በጉባዔው መካፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
§ በጉባዔው ላይ በአካል የምትገኙም ሆነ በባንኩ ዋና መ/ቤት ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡ ባለአክሲዮኖች ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚገልጽ ሕጋዊ ሰነድ (የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ) ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፣ እንዲሁም ሕጋዊ ውክልና ይዛችሁ የምትቀርቡ ተወካዮች የወካያችሁን ማንነት የሚገልጽ ሕጋዊ ሰነድ (የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ) አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
ራሚስ ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ
Leave a reply