ራሚስ ባንክ አ.ማ
ለራሚስ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ
ራሚስ ባንክ አ.ማ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል 2ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ያካሂዳል፡፡ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውም ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ያከናውናል፡፡
ይህ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9(3) መሠረት የታተመ ሲሆን የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔው በሚደረግበት ዕለት መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ዕጩ/ዎች መጠቆምና መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማ እና ምርጫ መስፈርት
- ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያገኘ እና አግባብነት ባለው የሥራ መስክ ቢያንስ የ7 ዓመት ልምድ ያለው፤
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ አና ለሥራው ተገቢ የሆነ ጊዜ መስጠት የሚችል፤
- በቢዝነስ ማኔጅምነት፣ ባንኪንግ፣ ፋይናንስ፣ አካውንቲንግ፣ ማኔጅምነት፣ ኢኮኖሚክስ፣ ሕግ፣ ቢዝነስ አድምንስትሬሽን፣ ኦዲት፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኢንቨስትመንት ማኔጅምነት እና ዘላቂነትን ጨምሮ የትምህርት ብቃት እና ልምድን ጨምሮ፣
- መልካም ሥነ-ምግባር ያለው እና ታማኝ የሆነ፣ እንዲሁም ከእምነት ማጉደል እና መሰል የወንጀል ድርጊቶች የጥፋት ውሣኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፤
- ከአራት ድርጅት/ተቋም በላይ በዳይሬክተርነት በማገልገል ላይ ያለ ሰው ሊመረጥ አይችልም፤
- በባንክ ሥራ ላይ ምክንያታዊ እና ተጨባጭ ውሣኔ መስጠት የሚችሉና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መረዳት እና መወጣት የሚችል፤
- በሥልጠና እና በተከታታይ አቅም በማጎልበት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት የሚችል፤
- አስቸጋሪ የቢዝነስ ጉዳዮችን የመመዘን፣ በመረጃ የተደገፈ ምክንያታዊ ውሣኔ የመስጠት፣ እንዲሁም የባንኩን ማኔጅመንት የውሣኔ ሃሳብ እና እርምጃ ገንቢ በሆነ መልኩ መተቸት የሚችል፤
- ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በአብሮነት መስራት የሚችል እና ጥሩ ተግባቦት ያለው፤
- ከዳይሬክተር የሚፈለጉ ግዴታዎችን ለመወጣት ከጥቅም ግጭቶች ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ፤
- የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው፤
- ዕድሜው ቢያንስ 30 ዓመት የሆነ፤ እና
- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎች ላይ የተገለጹት ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡
ልዩ ልዩ ሁኔታዎች፡
- ሁሉም ጥቆማዎች የተጠቋሚውን የትምህርት ብቃት እና ልምድ፣ እንዲሁም የጠቋሚውን ባለአክሲዮን ማንነት የሚገልጽ መሆን አለበት፣
- ባለአክሲዮን የሆነ ሰው እራሱን ሊጠቁም ይችላል።
- የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት አግባብነት ባላቸው የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ሊመረጥ ይችላል።
- አሁን ያሉ ዳይሬክተሮች ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በድጋሜ ሊመረጡ ይችላሉ።
- ቢያንስ 2 (ሁለት) ሴት ዳይሬክተሮች ሊኖሩ ያስፈልጋል።
- የራሚስ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ 13 አባላት ይኖሩታል፡፡
- 1/3ኛ የቦርድ አባላት ተጽዕኖ ፈጣሪ ካልሆኑ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሆኖ ጥቆማና ምርጫ ተጽኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ ይደረጋል፡፡
- 1/3ኛ የቦርድ አባላት ከሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሆኖ ጥቆማና ምርጫ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ይደረጋል።
- 1/3ኛ የቦርድ አባላት ገለልተኛ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሲሆኑ በነባሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተመልምለው የሚቀርቡ ሆኖ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ይመረጣሉ፡፡
ማስታወሻ፡– ማንኛውም በወንድ ጾታ የተቀመጠ አገላለጽ ሁሉ የሴትንም ጾታ ይጨምራል፡፡
የማህበሩ ጸሀፊ ራሚስ ባንክ አ.ማ
Leave a reply