Welcome to Rammis Bank Official SIte
Use Rammis Bank USSD Banking *678#
+25111-562-1202
info@rammisbank.et
Facebook Instagram Tiktok Telegram
  • Home
  • About us
    • Company Profile
    • Organizational Structure
    • Board Directors
    • Sharia Board
    • Executive Management
  • Our Services
    • DIGITAL BANKING
      • USSD
      • Mobile Banking
      • Internet Banking
    • RETAIL BANKING
      • Wadia Savings Account
      • Hajj Saving Account
      • Investment Account
        • Fixed Term Deposit
        • Flexi Term Deposit
      • Temporary Saving Account
      • Foreign Currency Saving Account
    • FINANCING
      • Muderabah & Musheraka
      • Murabaha
      • Ijarah
      • Istisnaa
    • RETAIL BANKING
      • Domestic Banking
      • International Banking
  • Media
    • NEWS & PRESS RELEASE
    • ANNUAL REPORTS
    • INTERNATIONAL STANDARDS
    • GALLERY
  • Contact us
  • Vacancy
Search

2ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ

November 18, 2024 /Posted byRBSystem Admin / 794 / 0

ራሚስ ባንክ አ.ማ

ለራሚስ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ መስፈርት ለማሳወቅ የወጣ ማስታወቂያ

ራሚስ ባንክ አ.ማ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል 2ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ያካሂዳል፡፡ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውም ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ያከናውናል፡፡

ይህ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና ምርጫ መስፈርት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ መመሪያ ቁጥር

SBB/91/2024 አንቀጽ 9(3) መሠረት የታተመ ሲሆን የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔው በሚደረግበት ዕለት መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ዕጩ/ዎች መጠቆምና መምረጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማ እና ምርጫ መስፈርት

  1. ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ እውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያገኘ እና አግባብነት ባለው የሥራ መስክ ቢያንስ የ7 ዓመት ልምድ ያለው፤
  2. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ አና ለሥራው ተገቢ የሆነ ጊዜ መስጠት የሚችል፤
  3. በቢዝነስ ማኔጅምነት፣ ባንኪንግ፣ ፋይናንስ፣ አካውንቲንግ፣ ማኔጅምነት፣ ኢኮኖሚክስ፣ ሕግ፣ ቢዝነስ አድምንስትሬሽን፣ ኦዲት፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኢንቨስትመንት ማኔጅምነት እና ዘላቂነትን ጨምሮ የትምህርት ብቃት እና ልምድን ጨምሮ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ከሆነ በኋላም በፋይናንስ ትንተና፣ በኮርፖሬት አስተዳደር፣ ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ሪስክ ማጅመንት፣ እና ኢንተርናል ኮንትሮል ዘርፎች ሥልጠና መውሰድ የሚችል
  4. በዜግነት ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች ገለልተኛ ዳይሬክተር ሆነው እንዲያገለግሉ ሊመረጡ ይችላሉ።
  5. ገለልተኛ ዳይሬክተር በባንክ፣ በሂሳብ አያያዝ፣ ከኦዲቲንግ፣ ከፋይናንስ፣ ከቢዝነስ አስተዳደር፣ ከኢኮኖሚክስ፣ ከህግ፣ ከቴክኖሎጂ እና ተዛማጅ የትምህርት ዘርፎች ከታወቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሁለተኛ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ሙያዊ ብቃት ሊኖረው ይገባል።
  6. ገለልተኛ ዳይሬክተር በፋይናንሺያል ዘርፍ ወይም ከፋይናንሺያል ሴክተሩ ጋር በተያያዘ በማስተማር/በማማከር፣ ወይም በኦዲት ወይም በስጋት አስተዳደር ወይም በማናቸውም አግባብነት ባላቸው የሥራ ዘርፎች ቢያንስ አሥር (10) ዓመታት የሙያ ልምድ ሊኖረው ይገባል።
  7. መልካም ሥነ-ምግባር ያለው እና ታማኝ የሆነ፣ እንዲሁም ከእምነት ማጉደል እና መሰል የወንጀል ድርጊቶች የጥፋት ውሣኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፤
  8. ከአራት ድርጅት/ተቋም በላይ በዳይሬክተርነት በማገልገል ላይ ያለ ሰው ሊመረጥ አይችልም፤
  9. በባንክ ሥራ ላይ ምክንያታዊ እና ተጨባጭ ውሣኔ መስጠት የሚችሉና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መረዳት እና መወጣት የሚችል፤
  10. በሥልጠና እና በተከታታይ አቅም በማጎልበት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት የሚችል፤
  11. አስቸጋሪ የቢዝነስ ጉዳዮችን የመመዘን፣ በመረጃ የተደገፈ ምክንያታዊ ውሣኔ የመስጠት፣ እንዲሁም የባንኩን ማኔጅመንት የውሣኔ ሃሳብ እና እርምጃ ገንቢ በሆነ መልኩ መተቸት የሚችል፤
  12. ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር በአብሮነት መስራት የሚችል እና ጥሩ ተግባቦት ያለው፤
  13. ከዳይሬክተር የሚፈለጉ ግዴታዎችን ለመወጣት ከጥቅም ግጭቶች ነጻ እና ገለልተኛ የሆነ፤
  14. የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ለማስጠበቅ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው፤
  15. ዕድሜው ቢያንስ 30 ዓመት የሆነ፤ እና
  16. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ መመሪያዎች ላይ የተገለጹት ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡

ልዩ ልዩ ሁኔታዎች፡

  • ሁሉም ጥቆማዎች የተጠቋሚውን የትምህርት ብቃት እና ልምድ፣ እንዲሁም የጠቋሚውን ባለአክሲዮን ማንነት የሚገልጽ መሆን አለበት፣
  • ባለአክሲዮን የሆነ ሰው እራሱን ሊጠቁም ይችላል።
  • የሕግ ሰውነት ያለው ድርጅት አግባብነት ባላቸው የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ሊመረጥ ይችላል።
  • አሁን ያሉ ዳይሬክተሮች ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በድጋሜ ሊመረጡ ይችላሉ።
  • ቢያንስ 2 (ሁለት) ሴት ዳይሬክተሮች ሊኖሩ ያስፈልጋል።
  • ከማህበሩ ጸሀፊ በስተቀር ቢበዛ 2 (ሁለት) የባንኩ ሠራተኞች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆነው ሊመረጡ ይችላሉ፣ ይሁን እንጂ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር መሆን አይችሉም።
  • የራሚስ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ 13 አባላት ይኖሩታል፡፡
  • 1/3ኛ የቦርድ አባላት ተጽዕኖ ፈጣሪ ካልሆኑ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሆኖ ጥቆማና ምርጫ ተጽኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ ይደረጋል፡፡
  • 1/3ኛ የቦርድ አባላት ከሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሆኖ ጥቆማና ምርጫ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ይደረጋል።
  • 1/3ኛ የቦርድ አባላት ገለልተኛ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሲሆኑ በነባሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተመልምለው የሚቀርቡ ሆኖ በሁሉም ባለአክሲዮኖች ይመረጣሉ፡፡

ማስታወሻ፡– ማንኛውም በወንድ ጾታ የተቀመጠ አገላለጽ ሁሉ የሴትንም ጾታ ይጨምራል፡፡

የማህበሩ ጸሀፊ
ራሚስ ባንክ አ.ማንክ አ.ማ

Share Post
Yaa’ii waliigalaa idilee...
IBSA ADEEMSA KENNIINSA EERUU B...

Related posts

ANNUAL REPORT2023/24

January 3, 2025 0
Continue reading

BOARD OF DIRECTORS ELECTION RESULT

December 23, 2024 0
Continue reading

IBSA ADEEMSA KENNIINSA EERUU BOORDIIDAAYIREKTAROOTAA / የዳይሬክተሮች ቦርድ የጥቆማ አካሄድ መግለጫ

November 25, 2024 0
Continue reading

Yaa’ii waliigalaa idilee fi ariifachiisaa abbootii aksiyoonaa 2ffaa

November 18, 2024 0
Baankii Raammis W.A Abbootii Aksiyoonaa Baankii Raammis Hundaaf Beeksisa Ulaagaa eeruu kennuu fi filannoo miseensota boordii daayirektarootaa beeksisuuf bahe Baankiin Raammis yaa’ii waliigalaa idilee fi... Continue reading

Leave a reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked

Blog Categories

  • Latest Updates (5)
  • News (11)
  • Terms and Tarrifs (1)
Flow to the hightest

Rammis Bank

Rammis Bank S.C., a fully-fledged interest-free bank in Ethiopia, was established on October 04, 2022, with a vision to become the hub of interest-free banking in East Africa.

  • Quick Links

    • Home

      Hot
    • About Us

    • Our Services

    • More Info

    • Vacancy

    • Contact Us

Contact Us

Bole Main Road, Flamingo Area, Rammis Tower

011-562-1202

info@rammisbank.et

www.rammisbank.et

Dial *678# for USSD

Follow Us

Facebook Instagram Tik-tok Telegram

Signup Newsletter

Copyright © 2025 Rammis Bank S.C. All rights reserved.

Terms and Conditions
Privacy Policy